የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከህወሓት ጋር በኡጋንዳ ሊወያዮ ነው የሚለው መረጃ የተሳሳተ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከህወሓት ጋር በኡጋንዳ ሊወያዮ ነው የሚለው መረጃ የተሳሳተ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከህወሓት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እየተነገረ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ተነገረ።

በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የገለጸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይል ነው።
የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራ የሚገኝ በመሆኑ በምንም መንገድ ወደ ድርድር እንደማይገባ ሕዝብ ይወቅልኝ ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ የመንግሥትን አቋም ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY