ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ህግ የማስከበር ግዳጅ ላይ ላለው የመከላከያ ሠራዊት የሕክምና ድጋፍ የሚሰጥ የሐኪሞች ቡድን ዛሬ ወደ ሥፍራው ተጓዘ።
የሐኪሞች ቡድኑ ከአዲስ አበባ ሲነሳ የከተማ አስተዳደሩ ሽኝት አድርጎለታል። በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ ጦር ግንባር ላቀኑት የሕክምና ባለሙያዎች የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ለማሟላት የከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋልተ
ሠራዊቱን በሙያው ለማገዝ ከተሰናዳው የጤና ባለሙያዎች ቡድን መካከል የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ 10 ስፔሻሊስት ሐኪሞችና 24 ነርሶች እንደሚገኙበት ታውቋል።