አሁን ይህን ፅሁፍ በምፅፈበት ሰዓት የአቦይ ፀሃዬ ሁለት ልጆች በካናዳ ይማራሉ ||...

አሁን ይህን ፅሁፍ በምፅፈበት ሰዓት የአቦይ ፀሃዬ ሁለት ልጆች በካናዳ ይማራሉ || አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል

አሁን ይህን ፅሁፍ በምፅፈበት ሰዓት የአቦይ ፀሃዬ ሁለት ልጆች በካናዳ ይማራሉ፤ የደህንነት ሀላፊ የነበረው የጌታቸው አሰፋ ሁለት ልጆች እዚህ አሜሪካን ሃገር ይማራሉ ። የነዝህን ባለስልጣናት ልጆች ጉዳይ በዝርዝር ስለማውቅ ጠቀስኩኝ እንጂ የአብዘኞቹ የህዋሃት ባላስልጣናት ልጆች ውጪ እንደሚማሩ/እንዳሉ/ የሚታወቅ ነው። ይህ ሆኖ እያለ እነዝሁ የህወሃት ባለስልጣናት የትግራይ የገበሬ ታዳጊ ልጆችን ለጦርነት ሲማግዱና የዚያን ህዝብ ስቃይ ሲያበዙ ማየት ልብ ይሰብራል።

አንድ እዝህ መፃፍ ከማያስፈልገኝ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የጌታቸው አሰፋ ሁለቱም ልጆች እዝሁ አሜርካን ሃገር ስንት ዶላር በየሩ እየተከፈለላቸው እንደሚማሩ ፤ የት እንደሚማሩ እና የገንዘብ ምንጮችን የሚያሳዩ ዝርዝር ሰነዶችን ለማየት ችዬ ስለነበር ስለልጆቹ አነሳሁኝ እንጂ በእኔ የግል የፖለቲካ አቋሜ ምክንያት ልጆቼ መወቀስ እንደሌለባቸው እንደማምን ሁሉ የጌታቸውም ሆነ የአቦይ ፀሃዬ ልጆች ለአባቶቻቸው ጥፋት መነቀፍ ስለሌለባቸው ስማቸዉንም ሆነ ሌላ ዝርዝር ስለልጆቹ ማንሳት አለስፈለገኝም ። ዋናው ነገር፤ እነ ጌታቸው ልጆቻቸው የማይዋጉትን ጦርነት በመቀስቀስ የትግራይን ህዝብ ለእልቅት መዳረግ እጅግ አሳዘኝ ተግባር መሆኑን ለመግለፅ ያህል ነው። በሌላ ሰው እጅ አሳት መጨበጥ …..

ጉዳዩን ህዋሃቶች አክርረው እዚህ ደረጃ እንዳያደርሱ በግልም ሆነ በድርጅቶች በኩል ሁኔታዎች ከሚፈቅዱት በላይ ከጣሩት ሰዎች አንዱ ስለሆንኩኝ ህዋሃትን ለማውገዝ ሙሉ ድፍረት ኣለኝ (ግጭቱ ከመጀመሩ 48 ሰኣታት በፊት እንኳ የህዋሃት ነባር ታገዮች ወደ ነበሩት ሰዎች ኢትዮጵያ ስልክ ደውዬ ጉዳዩን ማርገብ ይቻል እንደሆነ ቀዳዳ ፍላጋ በሰፊው አውርተን ነበር፤ እራሳቸው ምስክርነት መስጠት ይችላሉ)። ታዲያ– ወገኔ፤ ሃገሬ ብሎ አጠገቡ የተኘውን የመከላከያ ሰራዊትን እንደ ወራሪ ሃይል ቆጥሮ፤ ምንም ሳያደርጉት ምናባዊ ጠላት ፈጥሮ “ . . . መብረቃዊ እርምጃ ወሰድኩባቸው . . .” ከምል ሀላፊነት ከጎደለው ሃይል ጋር ድርድር ብሎ ማሰብ የማይቻል ነገር ነው። ህይወቱን ልሰዋለት፤ከጠላት ልጠብቀው ሰፈሩ ድረስ የሄደውን እና በተግባርም የሞተለትን መከላከያ ሰራዊት “ጠላቴ ነው” ቢሎ የሚያስብ ሃይል፤ ስለሌሎቻችን ምን ሊያስብ እንደሚችል መገመት ይከብደኛል። “ለህግ ይቅረቡልን!” ከማለት ውጭ ሌላ ምንም የምንለው የለም።

አሁን ጉዳዩ በእርቅ እና በድርድር ከሚያልቅበት አልፎ የሄደ መሆኑን በድፍረት መናገር ይቻላል። ከህግ በላይ መኖርን ባህላቸው ላደረጉት ህዋሃቶች በህግ መገዛትና ተንበርካክነት ተቀላቅሎባቸዋል። ለህግ ሁላቸንም ተንበርካክዎች ነን።

LEAVE A REPLY