ኡሁሩ ኬንያታ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ችግር በሰላም የሚፈታበት መንገድ እንዲፈለግ ጠየቁ

ኡሁሩ ኬንያታ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ችግር በሰላም የሚፈታበት መንገድ እንዲፈለግ ጠየቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከአቶ ደመቀ ጋር በነበራቸው ውይይት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ችግር በሰላም የሚፈታበት መንገድ እንዲፈለግ መጠየቃቸው ተሰማ።

ህወሓት ሁኔታዎችን እንዲያረግብ ጥሪ ያቀረቡት ኡሁሩ ኬንያታ፤ ጦርነት ኢትዮጵያ በአካባቢው የነበራት የኢኮኖሚ እምርታ የሚሸረሽር መሆኑንም አስረድተዋል።
ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ ኬንያ ገብተው ከኡሁሩ ኬንያታ ከመነጋገራቸው በፊት ከዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በተለያዩ ሀገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY