የህወሓት 34 ግዙፍ የንግድ ድርጅቶች ታገዱ

የህወሓት 34 ግዙፍ የንግድ ድርጅቶች ታገዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አምባገነኑ የህወሓት ቡድን በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ያከማቸባቸው 34 የንግድ ድርጅቶች መታገዳቸው ተሰማ።

የህወሓት የማፊያ ቡድን አባላትና ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ሁኔታ ሀብት ያከማቹባቸው 34 የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሳገዱን የገለፀው ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ነው።
ከታገዱት የህወሓት የፋይናንስ ተቋማት መካከልም ሰሞኑን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዮ የድርጅቱ መጋዘኖችና ቢሮዎች ውስጥ በርካታ ከባድ መሣሪያዎች የተገኙበት ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ሥራዎች ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ፣ ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ ማኅበር ፣ ሜጋ ማተሚያ፣ ኤፈርት ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እንዲሁም ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢስነስ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።

LEAVE A REPLY