ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሌሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል ድርድር ለማስጀመር ወደ ኢትዮጵያ ገቡ።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሽምግልናን አስመልክቶ ያለውን አቋም አሁንም ባይቀየርም ኦባሳንጆ አዲስ አበባ መግባታቸውን የዘገበው ዓለም ዐቀፉ የሚዲያ ተቋም ኤ ኤፍ ፒ፤ “ድርድር ለማድረግ መሞከር ተጠያቂ ያለመሆን ሕገ ወጥነትን የሚያበረታታ ነው፤ ማንኛውም ሀገር ሮኬትና ሚሳዔል አለኝ ከሚልና ጥቃት ለመሰንዘር ከሚዝት ኃይል ጋር ቁጭ ብሎ አይወያይም” በማለት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የመንግሥታቸውን አቋም መግለጻቸውን ዘግቧል።
ናይጄሪያን የመሩት ኦባሳንጆ ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ መሆኑን ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል የገለጹት ቃል አቀባያቸው ፕሬዝዳንቱ ወደዚያ ያቀኑት ለድርድር እንደሆነከመናገራቸው ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።