የኢትዮጵያ ማዕድንና ነዳጅ ኮርፖሬሽን በአፋር ክልል የነበረው የጨው ማምረቻ በክልሉ መንግሥት ተቀማ

የኢትዮጵያ ማዕድንና ነዳጅ ኮርፖሬሽን በአፋር ክልል የነበረው የጨው ማምረቻ በክልሉ መንግሥት ተቀማ

Danakil Depression, Ethiopia

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአፋር ክልል ጨው ማምረቻ ይዞታውን እና ግብርም ይከፍልበት የነበረውን ቦታ በአፋር ክልል መንግሥት መቀማቱን የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅ እና ባዮ ፊውል ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ እንደገለፀው ከሆነ የአፋር ክልል ማዕድን ቢሮ “አልተጠቀማችሁበትም” በሚል ምክንያት የጨው ማምረቻ ቦታውን እንደተነጠቁ ለማወቅ ተችሏል።
በኢትዮጵያ  ማዕድን ነዳጅ እና ባዮ ፊውል ኮርፖሬሽን
 እቅድ መምሪያ ኃላፊ እና የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ይድነቃቸው ተፈራ፤ ከተቋቋመ ወደ 18 ዓመት ገደማ የሆነው  የጨው ማምረቻው በመንግሥት የሚተዳደር እንደሆነና 10 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ቦታ ተሰጥቶት አንደነበርም ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY