ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በምዕራብ ወለጋ ዞን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረገ ሥራ 177 የኦነግ ሸኔ አባላት እጅ ሰጥተዋል ተባለ።
አካባቢውን የልማት ቀጠና ለማድረግ እና የኦነግ ሸኔ ቡድንን ለማጥፋት በተሠራው ሥራ በርካታ የጦር መሳሪያ መያዙንና 177 የቡድኑ አባላትን ለመማረክ ተማርኳል ያሉት የምዕራብ ወለጋ ዞን የጸጥታ ሓላፊ አቶ አብዮ ምህረቱ ናቸው።
በተወሰደው እርምጃ 65 የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ሥር ሲውሉ አድፍጠው ውጊያ የከፈቱ ሌሎች 45 አባላት ደግሞ መደምሰሳቸውን ከሓላፊው ገለጻ መረዳት ተችሏል።