የመጨረሻው እርምጃ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚወሰድ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

የመጨረሻው እርምጃ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚወሰድ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የትግራይ ልዩ ኃይል ለህወሓት እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን ይልቅ እጁን ለመከላከያ  ሠራዊት በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ ተጠናቀቀ።

ጁንታውን ለመደምሰስ በተጀመረው እንቅስቃሴ ውስጥ በተሳሳተ ፖለቲካ የተጠለፈው የትግራይ ልዮ ኃይል በሰላም እጅ እንዲሰጥ የተቀመጠለት ጊዜ መጠናቀቁን በይፋ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ናቸው።
በቀረበው ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ምስጋና ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁን ግን የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ጥቂት ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር እንደሚካሄድ ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY