በኢትዮጵያ ለዕጩ አሽከርካሪዎች ከሚዘጋጁት 3 ሺኅ የምዝና ጥያቄዎች 800 ያህሉ የተሳሳቱ ነበር...

በኢትዮጵያ ለዕጩ አሽከርካሪዎች ከሚዘጋጁት 3 ሺኅ የምዝና ጥያቄዎች 800 ያህሉ የተሳሳቱ ነበር ተባለ

ADDIS ABABA, ETHIOPIA - APRIL 4 : Ethiopian Transport Minister Dagmawit Moges speaks during a press conference on "Boeing 737 Max 8" crash in Addis Ababa, Ethiopia on April 4, 2019. (Photo by Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ለዕጩ አሽከርካሪዎች ከሚዘጋጁት ሦስት ሺኅ የምዘና ወይም የብቃት ማረጋገጫ ጥያቄዎች ውስጥ 800 ያህሉ የተሳሳቱ እንደነበሩ ታወቀ።

ትራንስፖርት ሚኒስትር ከዘርፉ አመራሮች፣ ከአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ እና ተሸከርካሪ ምርመራ ተቋማት ባለቤቶች ጋር በተወያየበት መድረክ ላይ ነው ለዕጩ አሽከርካሪዎች ከሚዘጋጁት ሦስት ሺኅ የምዘና ጥያቄዎች መካከል 800 ያህሉ የተሳሳቱ እንደነበሩ የተነገረው።
በምክክር መድረኩ የምዘና ፈተናዎቹ የተለያዩ ክፍተቶች እንዳሉባቸው የተነገረ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ ሙሉ በሙሉ የምርጫ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች፤ አራቱም አማራጮች መልስ የማይሆኑበት ወይም አራቱም መልስ የሚሆኑበት ሁኔታ እንዳለ ተገልጿል።
በአማራጮቹ ላይ ሁሉም መልስ ይሆናሉ፣ አሊያም አይሆኑም ተብሎ የተገለፀ ነገር አለመኖሩ ጥያቄዎቹን መልስ አልባ እንዳደረጋቸው በመነገሩ ይህ ሠፊ ክፍተት በፍጥነት ማሻሻያ እንዲደረግበት ሐሳብ ቀርቧል።

LEAVE A REPLY