አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ሕዝብ ከቤቱ ወጥቶ ጦርነቱን እንዲቀላቀል አሳሰበ

አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ሕዝብ ከቤቱ ወጥቶ ጦርነቱን እንዲቀላቀል አሳሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ በሁሉም ቦታዎች ድል እየቀናው መሆኑን ያመኑት የህወሓት ሊ/መንበር ዶክተር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የትግራይ ሕዝብ በጠቅላላ ወጥቶ ጦርነቱን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል።

የትግራይ ልዮ ኃይል በሦስት ቀናት ውስጥ እጁን እንዲሰጥ የቀረበለት ጊዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ ከትናንት ጀምሮ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች መከላከያ ሠራዊቱ ድልን እነተጎናጸፈ መሆኑ የህወሓት አመራሮችን ክፉኛ አስደንግጧቸዋል።
ዛሬ ረፋድ ላይ በድምፀ ወያኔ ላይ ቀርበው መከላከያ ሠራዊቱና የአማራ ልዮ ኃይል ራያና ሽረን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸውን የተናገሩት ደብረፂዮን፤  ” ይህ ድል ጊዜያዊ ነው” ሲሉም የታጣቂዎቻቸውን ሽንፈት ለመሸፋፈን ሞክረዋል።
የመጨረሻው ሰዐት ላይ የሚገኙት ደብረፂዮንና አባሎቻቸው ወራሪ የባዕዳን ጦር ነመጣባቸው ይመስል የትግራይ ሕዝብ ሁሉም ከቤቱ ወጥቶ ጦርነቱን እንዲቀላቀልና እንዲዋጋ ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY