የዛሬ 20 አመት ገደማ፣ ህወሃትን በሚመለከት አንድ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ። ትህነግ ከዲሞክራሲ፣ ከሰብአዊ መብት እና ከፍትህ ጋር የተጣላ፣ ለሱ አሜን ብሎ የማይገዛውን ከምድረ-ገጽ በማጥፋት የሚያምን ድርጅት መሆኑን አመንኩበት።
ታድያ ፈረንጆቹን ለማሳመን በእንግሊዝኛው እንዲህ ብዬ የኢትዮሚድያ ቀዳሚ መርህ አረኩት! – “TPLF cannot be reformed. Like apartheid, it should be dismantled.” ግርድፍ ትርጉሙ – “ህወሃት ሊዘምን ፈፅሞ አይችልም።
እንደ አፓርታይድ፣ ከሥሩ ተነቅሎ መጣል አለበት!” የሚል ነበር።
ታድያ ተሳሳትኩ እንዴ? የትግራይ ህዝብ ሆይ – ክብርህን ገፎ ሲያዋርድህ ከኖረው ክፉ ጠላት ነፃ የምትወጣበት ቀን ተቃርቧል። ትህነጎች ልጆቻቸውን አሜሪካና አውሮፓ በቅንጦት እያኖሩ አንተንና ልጅህን ቤዛ ሊያደርጉ ለሌላ እልቂት ጥሪ አቅርበውልሃል። ስንት ጊዜ ይግደሉህ? በቃኝ በላቸው። እጅህ ላይ መሣሪያ ካለ፣ ከሀገርህ መከላከያ ኃይል ጎን ቁመህ፤ እነ ህወሃቶች ላይ አዙረህ፣ “እንዳትበላሽ፣ እጅ ወደላይ!” በልልኝ። ድልህን ከሀገርህ ልጅ ጋር አብስር!
ድል ለኢትዮጵያ!