ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትግራይ ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነው የትግራይ የሚገኘው የህዋሃት ቡድንን ክፉኛ ወቀሱ።
ኤርትራን በሚመለከት ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በፍጥነት በትዊተር ገጻቸው ላይ በማጋራት የሚታወቁት የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል፤ ጦርነቱ ከተጀመረ ከሦስት ሳምንት በኋላ በኤርትራ መንግሥት በኩል ያለውን አቋም ዘግይተውም ቢሆን ገልጸዋል።
ግልጽ ባልሆነ መንገድ የሰፈረው የየማነ ገብረመስቀል የትዊተር መልእክት፤ “ተገማች የሆነ ገነር ግን ውጤት አልባ የመጨረሻ መፍጨርጨርን ማጉላት አስፈላጊ አይደለም” የሚል ጽሑፍን አካቷል።
ሁለቱ ኃይሎች ወደ ጦርነት ባመሩበት ወቅት የትግራይ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ኤርትራ የኢትዮጵያ ሠራዊትን እየደገፈች ነው ሲል ተደጋጋሚ መውቀሱ አይዘነጋም።