ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የቀድሞው የህወሓት ሹማምንት የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓትን የሚደግፍ የማግባባት ሥራ አከናውነዋል ተብለው ተከሰሱ።
የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቴዎድሮስ አድኃኖም የኢትዮጵያውያንን ውለታ ክደዋል በማለት ከሰዋቸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ላይ የቀረበውን ክስ አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጡ ቢቢሳ ጥያቄ ቢያቀርብላቸውም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዐት ድረስ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጡም።
“ህወሓትን ለመደገፍና የጦር መሳሪያ እንዲያገኝ ለማድረግ ዶ/ር ቴዎድሮስ ያልፈነቀሉት ድናጋይ የለም” ያሉት ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፤ “ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመው እነዚህን ሰዎች ያወግዛሉ ብለን አንጠብቅም። እነሱን ለመደገፍ ሁሉንም ነገር ሲያደርጉ ነበር፤ ጎረቤት ሀገራት ጦርነቱን እንዲያወግዙ ሲቀሰቅሱ ነበር” ሲሉም በይፋ ተችቷቸዋል።