ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሓት ቡድን አመራሮች ከድርጊታቸው ተቆጥበው በሰላም እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበላቸው።
በቅርቡ ስም ዝርዝራቸው የተገለጸውና የፍርድ ቤት መያዣ የወጣባቸው የህወሓት ሹማምንት አሁን ላይ መቀሌ ውስጥ ያሉበት ቦታ በመከላከያ ሠራዊቱ መረጋገጡን ተከትሎ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ተጠይቀዋል።
ይሁን እንጂ አሁንም የህወሓት ቡድን ህግን ከማክበር ይልቅ ታጣቂ ኃይሉ ጥፋት እንዲወስድ ተደጋጋሚ ጥፋቶችን በመፈጸም ላይ ይገኛል። እየወጡ ያሉ የተለያዮ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ሠራዊቱ የመጨረሻውን ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጁ እንደሆነና አየር ኃይሉም የጁንታው አባላት የሚገኙበትን ቦታ በመለየቱ እርምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል።