ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም የቀረበባቸውን ክስ አስተባበሉ

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም የቀረበባቸውን ክስ አስተባበሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ህወሓትን በመደገፍ ኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ልቤን ነክቶኛል ያሉት ዶክተር ቴዎድሮስ፤ “በዚህ ውስጥ አንድ ወገንን እንደደገፍኩ የሚገልጹ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል። ነገር ግን ይህ እውነት አይደለም” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስነብበዋል።
 “እኔ የምደግፈው አንድ ወገን ቢኖር ሠላም የሚመጣበትን መንገድ ብቻ ነው” በማለት ከተለያየ አቅጣጫ እየቀረበባቸው ያለውን ወቀሳና ትችት ያጣጣሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ በጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ ከማድረጋቸው ባሻገር፤
ሁሉም ወገኖች ለሰላም እንዲሠሩና የሰላማዊ ሰዎች ደኅንነት ተጠብቆ የጤናና የሰብአዊ ድጋፍ የሚያገኙበት መንገድ ሊመቻች ይገባል ብለዋል።

LEAVE A REPLY