ሀሙስ “የሀገር ልጅ፣ የማር እጅ” በሚል መርህ በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን የሚደግፍ ፕሮግራም...

ሀሙስ “የሀገር ልጅ፣ የማር እጅ” በሚል መርህ በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን የሚደግፍ ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነው

 ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የፊታችን ሀሙስ  “የሀገር ልጅ የማር እጅ”  በሚል  መርህ በትግራይ ክልል የሚኖሩና በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት ችግር የደረሰባቸው ዜጎችን ለመደጎም የሚረዳ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል ተባለ።
በዚህ የድጋፍ መርኃ ግብር ላይ የጥበብ ባለሙያዎች በሙዳይ፣ አገልግል፣ ጥላ እና ነጠላ ዘርግተው ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያሰባስቡ ተነግሯል።
የብሔራዊ ቴአትር እና የሰላም ሚኒስቴር በጋራ በሚያከናውኑት በዚህ መርኃግብር አርቲስቶች፣ አትሌቶች፣ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ሁሉ በተቋማት አካባቢ፣ ድርጅቶችን እና ፋብሪካዎችን ጨምሮ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል በማማከል የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚሰበስቡ ከደረሰን መረጃ መረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY