ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲሰፍን እና ዜጎቻችን ከጉዳት እና እጦት ነፃ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ ነገር መንግሥታቸው እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።
ሕግ በማስከበር ተልዕኮው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያስመዘገበው ድል የሚደነቅ ነው በማለት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሠራዊቱ ትናንት ምሽት በአዲግራት ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች ተቆጣጠሮ ካደረ በኋላ ዛሬ ደግሞ አዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ ከጽንፈኛው ህወሓት ኃይል ነፃ እንዳወጣ አረጋግጠዋል።
የፌዴራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው ከተማዎች እና አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች በፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ወደ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው መመለስ መጀመራቸውንም የብልፀግናው መሪ ዛሬ ይፋ አድርገዋል።