ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ሰርቪስ ተሽከርካሪዎችን እነዲጠቀሙ የሚያስገድድ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ።
ተማሪዎቹ ሰርቪስ እንዲጠቀሙ የተባለው የትራፊክ መጨናነቅን ከማስቀረት አንጻር መሆኑን የጠቆመው መረጃ፤ የተማሪዎች መጓጓዧ ሰርቪስን ሁሉም ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።
ከፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ረቂቅ መመሪያው እንዲወጣ እየተሠራ መሆኑን የተናገሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ጅሬኛ ሄርጳ፤ ትምህርት ሲጀመር በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቅረፍ አንፃር ከፍተኛ ሚና አለው ተብሎ ታስቦ የቀረበ የመፍትሄ ሐሳብ ስለሆነ በተግባር ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሠራበት ነው ብለዋል።