ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የ4 ተጨማሪ ኩባንያዎች የባንክ ሒሳብ፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አገደ።
አስቀድመው ተመሳሳይ የእግድ ትእዛዝ የወጣባቸው 34 ድርጅቶችን ጨምሮ የታገዱት ኩባንያዎች ቁጥር 38 መድረሱን ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ፍቃዱ ፀጋ አረጋግጠዋል።
ከ38ቱ ኩባንያዎች መካከል በስም መመሳሰ፣ የኤፈርትን የኢሜል አድራሻ በመጠቀማቸው ከህወሓት ጋር ተዛምዶ ይኖራቸዋል በሚል ጥርጣሬ የባንክ ሒሳባቸው ታግደው ከነበሩት ኩባንያዎች ቢያንስ አንዱ ከዝርዝሩ ሊወጣ እንደሚችል ሓላፊው ተናግረዋል።
እገዳው በድርጅቶቹ ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ ሠራተኞችን ሕይወት እንዳያመሰቃቅል ለድርጅቶቹ አዲስ አስተዳደር ተሹሞላቸው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።