ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመጨረሻ ያሉትን የሦስት ቀን ገደብ ዳግም ለጁንታው አስቀመጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመጨረሻ ያሉትን የሦስት ቀን ገደብ ዳግም ለጁንታው አስቀመጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀለ ከተማ ውስጥ ያሉ አመራሮችና ኃይሎች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ የመጨረሻ ያሉትን የሦሰት ቀናት ቀነ ገደብ ዛሬ ይፋ አደረጉ።

የማያዳግም እድል በተባለለት የመጨረሻው ምዕራፍ  የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ወደ ክልሉ ዋና ከተማ በሚያደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት በሰው ላይና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የህወሓት አመራሮች፣ የልዩ ኃይሉና ለሚሊሻ አባላት እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
 ነዋሪው በመጨረሻው ዘመቻ ላይ ከሠራዊቱ ጋር በመተባበር ሊደርስ የሚችል ጉዳትን እንዲከላከል ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የህወሓት አመራሩና የትግራይ ኃይል እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ የ72 ሰዐታት የመጨረሻ የጊዜ ገደብ ማስቀመጣቸውን ይፋ አድርገዋል።
ከሳምንት በፊት ለልዩ ኃይሉ እና ሚሊሻ አባላት እጃቸውን እንዲሰጡ ተመሳሳይ ቀነ ገደብ አስቀምጠው ተቀምጦላቸው እንደነበር ይታወቃል።

LEAVE A REPLY