በሕዝብ ጥቆማ በአዲስ አበባ 343 ሰዎች በፖሊስ መያዛቸው ተነገረ

በሕዝብ ጥቆማ በአዲስ አበባ 343 ሰዎች በፖሊስ መያዛቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ከነዋሪዎች የደረሰ ጥቆማን ተከትሎ በተደረጉ ምርመራዎች ፤ በአዲስ አበባ 343 ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተሰማ።

መረጃውን ይፋ ያደረገው ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከእነዚህም መካከል 160 የሚሆኑት በዋስ መለቀቃቸውን አረጋግጧል።
ህግ አስከባሪው ፖሊስ የሚደርሱትን ጥቆማዎች ተከትሎ በሚያደረገው ፍታሻ ላይ ቅሬታዎች እየመጡ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶ/ር ጢሞቲዎስ፤ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የምንመለከት ከመሆኑ ባሻገር የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ ቅሬታ መቀበያ መንገዶችን እየዘረጉ እንደሆኑ አስረድተዋል።
የተዘጋጁ አስተያየት መቀበያ የስልክ መስመሮች እና ዴስኮች በተቋማቱ ይፋ እንደሚደረጉ የተናገሩት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፤ ደርሰዋል ተብለው የሚቀርቡ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ መንግሥት መርማሪዎችን እና ዐቃቤ ህጎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ማሰማራቱን አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY