ከትግራይ ወደ ሱዳን የሸሹ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 40 ሺኅ ደርሷል ተባለ

ከትግራይ ወደ ሱዳን የሸሹ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 40 ሺኅ ደርሷል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ከ40 ሺኅ በላይ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ይፋ አደረገ።

የተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የጠቆመው ድርጅቱ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻም 5 ሺኅ ተፈናቃዮች በምሥራቃዊ ሱዳን በኩል እንደገቡም ገልጿል።
UNHCRም ሆነ አጋር ድርጅቶቹ ምግብን ጨምሮ ህይወት አድን እርዳታዎችን እያደረጉ ቢሆንም የተፈናቃዮች ቁጥር በመጨመሩ የሰብዓዊ የእርዳታ የቁሳቁስ ችግርን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል።
የትግራይ ተፈናቃዮችን ለማስተናገድ በቂ መጠለያም እንደሌለ የገለጸው ዓለም ዐቀፍ የስደተኞች ተንከባካቢ ድርጅት፤ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ሕጻናት፣ ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ 300 የሚሆኑ ተፈናቃዮች የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ምግብም እየለገሰ እንደሚገኝና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ለማኅበረሰብ ክፍሎችም የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑን አረጋግጧል።

LEAVE A REPLY