የትህነግ አመራሮች እጅ እንዲሰጡ የቀረበውን ጥሪ እንደማይቀበሉ ይፋ አደረጉ

የትህነግ አመራሮች እጅ እንዲሰጡ የቀረበውን ጥሪ እንደማይቀበሉ ይፋ አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጁንታው አባላት እጃቸውን እንዲሰጡ ያስቀመጡትን የ72 ሰዐት ጊዜ ገደብ  እንደማይቀበሉት የህወሓት አመራሮች አስታወቁ።

ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ  ቴሌቪዥን ቀርበው የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ እንደማይቀበሉና በውጊያው እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በትግራይ በኩል ላሉ ኃይሎችና ለህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ ነገ ረቡዕ የሚያበቃ ቢሆንም፤ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በጠቅላይ ሚንስትሩ የተሰጠውን የጊዜ ገደብ እንደማይቀበሉና መታገላቸውን እንቀጥላለን ብለዋል።
 “እኛ ማን እንደሆንን አልተገነዘቡም፤ መርህ ያለን ሰዎች ነን። ክልላችንን እራሳችን ለማስተዳደር መስዋዕትነት እንከፍላለን” ሲሉ በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው በተስፋ መቁረጥ መንፈስ ውስጥ የታዮት የትህነግ ሹማምንት፤ የተለያዩ የትግራይ ከተሞች በአገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር መውደቃቸውን ቢያምኑም፤ “የፌደራሉ መንግሥት እንደሚለው ግን በህወሓት ኃይል ላይ ሽንፈት እየደረሰ አይደለም” በማለት ተከራክረዋል።

LEAVE A REPLY