የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተና (ማትሪክ) በድጋሚ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተና (ማትሪክ) በድጋሚ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና (ማትሪክ) ዳግም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

አሁን ላይ ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ፈተናው መራዘሙን የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ይፋ አድርገዋል።
አምና በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የ8ኛ ክልል ክልላዊ ፈተና ግን ከታኅሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት የሚወሰን በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው ወቅት ሊሰጥ እንደሚችልም ተሰምቷል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በይፋ የተገለፀ ነገር ባይኖርም ፤ የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ባሉ የሕግና ፀጥታን የማስከበር ሂደቶች መቋጫ እንዳገኙ እንደሚከናወን ሚኒስቴር ዲኤታው አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY