የህወሓት ሀብት ማካበቻ የነበረው ወጋገን ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት ተሾመለት

የህወሓት ሀብት ማካበቻ የነበረው ወጋገን ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት ተሾመለት

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የቀድሞ ወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አባይ መሐሪ በቦርድ መነሳታቸውን ተከትሎ ወ/ሮ ብርቱካን ገ/እግዚአብሔር የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ተሰማ።

ወ/ሮ ብርቱካን ከዚህ ቀደም የእናት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዮ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአቢሲኒያ ባንክም በከፍተኛ ሓላፊነት አገልግለዋል።
ወ/ሮ ብርቱካን የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በቦርዱ ታጭተው በብሔራዊ ባንክ በኩል ማረጋገጫ እስኪሰጣቸው ድረስ እየጠበቁ ከቆዮ በኋላ፤ ብሔራዊ ባንክም ወ/ሮ ብርቱካንን የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት እንደሆኑ መፍቃዱን ዛሬ በይፋ አረጋግጧል።

LEAVE A REPLY