ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሀገር መከላከያ ሠራዊት የመጨረሻ እና ሦስተኛ ምዕራፍ የተባለውን ዘመቻ በህወሓት አመራሮችና በትግራይ ኃይሎች ላይ እንዲፈጽም ትዕዛዝ መሰጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ አደረጉ።
የህወሓት አመራሮች እና ተዋጊ ኃይሎች እጃቸውን እንዲሰጡ ባለፈው እሁድ አስቀምጠውት የነበረው የተሰጠው የ72 ሰዐታት ጊዜ ገደብ መጠናቀቁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
ሕግ የማስከበሩ ዘመቻችን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፤ መከላከያ ሠራዊት የመጨረሻውን እና ሦስተኛውን የዘመቻ ምዕራፍ እንዲፈጽም ትዕዛዝ መሰጠቱን አረጋግጠዋል።