ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገጽ ለገጽ ትምህርት ህዳር 21 እና 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ይፋ አደረገ።
በግል ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 21 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የገለጸው ትምህርት ቢሮ፤ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ የትምህርት አሰጣጡ ህዳር 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር አስታውቋል።
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25 እንደሚሰጥም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ ገልጸዋል።