ዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ...

ዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ሊከበር ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዓለም ዐቀፍ የሰብኣዊ መብቶች ቀን በኢትዮጵያ ውስጥ በማረሚያ ቤቶች ሊከበር መሆኑ ተሰማ።

ዓለም ዐቀፍ የሰብኣዊ መብቶች ቀን ከታህሳስ 1 /2013 ዓ.ም ጀምሮ “ለሰብኣዊ መብቶች ተግባራዊነት በመትጋት ዓለማችንን በተሻለ መልሰን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በዓለም ዐቀፍ ደረጃ እንደሚከበር መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም ከኀዳር 22 እስከ 30 ባሉት ቀናት በተለያዮ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን፤ ዘንድሮም ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሊቲ በሚገኘው የፌደራል ማረሚያ ቤት እንደሚከበር ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY