የመቀሌ ስትራቴጂክ ቦታዎች በዚህ ሰዐት ዙሪያውን በታንክ መከበባቸው ይፋ ተደረገ

የመቀሌ ስትራቴጂክ ቦታዎች በዚህ ሰዐት ዙሪያውን በታንክ መከበባቸው ይፋ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሀገር መከላከያ ሠራዊት በአሁኑ ሰዐት መቀሌን እና የወንጀለኛው ጁንታ ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር  የሚያስችሉ  ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን ይፋ አደረገ።

ሠራዊቱ ሀውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲቀየህ፣ ማይመሳኖን እና ውቅሮን ከጁንታው ታጣቂ ሃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ ማድረጉን የገለጹት በመከላከያ ሠራዊት ሕብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሓላፊ ሌተናል ጀነራል ሀሰን ኢብራሂም፤ ህግ የማስከበር ሂደቱ በውጤታማነት ቀጥሎ ተጨማሪ  የትግራይ ክልል ከተሞችን ከጁንታው ታጣቂ ነፃ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።
 በአድዋ ግንባር የተንቀሳቀሰው ሠራዊት ሃውዜን፣ አብርሃ ወአፅበሃንና ውቅሮን የተቆጣጠረ ሲሆን፤  አጉላን በግማሽ ቀን መቆጣጠር ችሏል። በአሁኑ ወቅት በመቀሌ አቅራቢያ ወደሚገኘው መሰቦ ተራራ እየገሰገሰ በመሆኑ መቀሌን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመቆጣጠር እንደሚችል ተነግሯል።
በሁለተኛው ግንባርም በአዲግራት በኩል ሳንቀጣ እና አልነጃሺን በመቆጣጠር የሀገር መከላከያ ሠራዊት ውቅሮ ገብቷል ያሉት ጀነራሉ፤ በሦስተኛው የራያ ግንባር ደግሞ አዲቀይህን የተቆጣጠረ ከመሆኑ ባሻገር፣ ሄዋናና በመያዝ ሁሉንም ምሽጎች ሰባብሮ ወደፊት እየተጓዘ ነው ብለዋል።
በማጠቃለያው ምዕራፍ መቀሌን ለመቆጣጠር የሚያስሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች በሠራዊቱ ተይዘው መቀለ ከተማ ዙሪያዋን በታንክ ተከባለች ያሉት ጀነራሉ፤ ጁንታው በጉላን በኩል መንገድ ለመዝጋት ቢሞክርም እንዳልተሳካለትና ወደ ኋላ ማፈግፈጉን አጋልጠዋል።

LEAVE A REPLY