“እኔን የሚማርከኝ ኢትዮጵያዊነት ነው” ያሉት ጀነራል ባጫ ደበሌ በመቀሌ የቤት ለቤት አሰሳ...

“እኔን የሚማርከኝ ኢትዮጵያዊነት ነው” ያሉት ጀነራል ባጫ ደበሌ በመቀሌ የቤት ለቤት አሰሳ ተጀምሯል አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከውሸት ጋር የኖረው የወያኔ ተሸናፊ ኃይል 30 ታንኮችና ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌን ማርኪያለሁ ማለቱ ጁንታው ምን ያህል የወረደ በድን መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተመላሹ የጦር ሜዳ ጀግና ጀነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ።

“እኔን የሚማርከኝ ኢትዮጵያዊነት መሆኑን አለማወቁ ነው ወያኔን በውሸት ያስቀባጠረው” ያሉትሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ፤ በአዛዥነት ከፍተኛ ድል ባስመዘገቡበት የራያ ግንባር ጦር ሜዳ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

 ለተማረከና ተሸንፎ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ብቻ ነፍስ ያለው የህወሓት ማፊያ ቡድን ፤ ትናንት ታንኮችንና ባጫ ደበሌን ማርከናን ብሎ ያሰራጨው ወሬ ቡድኑ ወደ ተራ አሉቧልት መውረዱና መግቢያ ማጣቱን ያሳያል እንደሆነም ተናግረዋል።
“እኔ በምመራው ግንባር ጁንታው አሰማርቷቸው የነበሩና ተበታትነው የቀሩትን ኃይሎች የመሰብሰብና የማጣራት ሥራ እያከናወንን ነው” በማለት ሠራዊቱ አሁን የሚገኝበትን ደረጃ ያመላከቱት ጀነራል ባጫ ደበሌ፤ መቀሌ ከተማ ውስጥ ተበትኖ ያለው የማፊያ ቡድኑ ታማኞች የሽብር ተግባር ለመፈፀም እንደሚንቀሳቀስ በመታወቁ ፣ የቤት ለቤት አሰሳና የማጣራት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

LEAVE A REPLY