የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የጁንታው አባላትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሠራ መሆኑን ገለጸ

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የጁንታው አባላትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሠራ መሆኑን ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የህወሓት ጁንታ አስቦት የነበረው ሀገር የማፍረስ ህልም መክሸፉን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።

የጥፋትቡድኑን ለመቆጣጠር እስካሁን በተመዘገበው ድልም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፈው ግዙፍ የደህንነት እና የፀጥታ ተቋም፤ ከሌሎች የመረጃና ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ድብቅ ሴራ በማጋለጥ ለህግ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ላይ ኃላፊነቱን ለመወጣት በትጋት እየሠራ መሆኑን ገልጿል።
የጁንታው ጉጀሌ በፖለቲካው አውድ የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ፣ ትግራይ ክልል በመመሸግ ህገወጥ ተግባራትን ሲፈፅም ቆይቷ ያለው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መግለጫ፤ ቡድኑ ጦርነቱን የጀመረው በግልፅ፣ በተደራጀ እና በከዳተኛ አባሎቹ ጭምር ተገቢ ጥናት ፈፅሞ የሠራዊቱን ቁልፍ ትጥቆች፣ ስንቆች፣ የማዘዣ ጣቢያዎችና የዕዝ ሰንሰለቶች ለመቆጣጠርና ለመበጣጠስ በማለም እንደነበርም አስረድቷል።

LEAVE A REPLY