የ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ ይደረግላቸዋል ተባለ

የ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ ይደረግላቸዋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

ከአንድ ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን ሦስት የትምህርት ሴሚስቴር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲልም ሚኒስትር መ/ቤቱ ገለጸ።
ተመራቂ ተማሪዎች በቀሪዎቹ አጭር ወራት ውስጥ ያልተጠናቀቁ የትምህርት እና ሥልጠና ተግባራትን በተቻለ ቅልጥፍና እና ዝግጁነት በማጠናቀቅ ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም እንዲቀላቀሉም ይደረጋል ነው የተባለው።
የከፍተኛ ትምህርት እና ሥልጠና ማኅበረሰብ በሙሉ የተለመደውን ቀና ድጋፍ እና ትብብር በማድረግ የ2013 ዓ.ም የትምህርት እና ሥልጠና ዘመን የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ቀርቧል።

LEAVE A REPLY