ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ነገ ይካሄዳል ተባለ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚገኘው መሰብሰቢያ አደራሽ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሚካሄደው ስብሰባ የተለያዮ አጀንዳዎች ይስተናገዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የም/ቤቱን 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ መርምሮ ማጽደቅ፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን መልስ ማዳመጥ ዋነኞቹ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።