ህወሓቶች ኃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የመንፈቅለ መንግሥት ለማድረግ አሲረው ነበር

ህወሓቶች ኃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የመንፈቅለ መንግሥት ለማድረግ አሲረው ነበር

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ለውጡ ከመጀመሩ በፊትና ከጀመረ በኋላም ከባድ ፈተናዎችን እንደተጋፈጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት የሀገሪቱን ከፍተኛ ሥልጣን ይዘው ከነበሩ የደኅንንትና የመከላከያ አመራሮች እርሳቸውን ጨምሮ ለውጥ እንዲመጣ ጥረት ሲያደርጉ በነበሩት ሰዎች ላይ ውንጀላዎች፣ ማሳደዶችና ግድያ የመፈጸም ሙከራ እንደነበር ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።
“ቲም ለማ” የሚል መጠሪያ የያዘው የለውጡ ቡድን ሥልጣኑን ለመጨበጥ ዳር ዳር እያለ ባለበት የመጨረሻ ሰዐት በስልጣን ላይ የበላይ ሆኖ ለመቀጠል ፍላጎት የነበረው ቡድን፤ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ለማደረግ ሲያሴር ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ሲያሳውቁ ደግሞ እየታዘዘ በታማኝነት ቦታውን የሚይዝ ሰው ለመተካት ጥረት መደረጉንም አስረድተዋል።
ይህንን ተከትሎ ከጁንታው ፈቃድ ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ ሰዎችን ተስፋ ለማስቆረጥና ለማስወገድ በደኅንነቱና በታጠቁ ወታደሮች ከባድ ክትትል ይደረግባቸው ሲሉ ሂደቱን ያስታወሱት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ ይህ ሁኔታ ያሰጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩና አጋሮቻቸው በገዢው ኃይል በወቅቱ እስር ወይም ግድያ ቢፈጸምባቸው ትግሉ እንዲቀጥል ያለውን ሁኔታ የሚያመልክቱ የቪዲዮና የጽሑፍ መልዕክቶች አዘጋጅተው በሚታመኑ ሰዎች እጅ እንዲቀመጥ እስከማድረግ መድረሳቸውንም አስታውሰዋል።

LEAVE A REPLY