ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው 2013 ዓመት በመጀመሪያ ሩብ ዓመት 44 ተሽከርካሪዎች መሰረቃቸው ተነገረ።
በተለይም በየካ ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች ከፍተኛ የስርቆት ድግግሞሽ ከተገመዘገበባቸው መካከል መሆናቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዘርፍ ኋላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ገልጸዋል።
ተሽከርካሪዎችን ጠባቂ በሌለባቸው አካባቢዎች ማቆም፣ የተሽከርካሪ ቁልፍን ውስጥ ጥለው በመሄድ እና የተሸከርካሪ መስታወትን ክፍት በማድረግ አብዛኛው የስርቆት ወንጀል እንደተፈጸመ የገለጹት ኢንስፔክተሩ፤
ፖሊስ የመኪና ስርቆት በመፈፀም ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መሀል ለፍርድ በማቅረብ እንዲቀጡ እንዳደረገና በቀሪዎቹ ላይ ደግሞ ምርመራ የማጣራት ሥራን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።