የጁንታው ሚሊሻ መሪ ሱዳን ውስጥ ከወታደሮቹ፣ ቤተሰቦቹና 5 ቢሊዮን ፓውንድ ጋር በቁጥጥር...

የጁንታው ሚሊሻ መሪ ሱዳን ውስጥ ከወታደሮቹ፣ ቤተሰቦቹና 5 ቢሊዮን ፓውንድ ጋር በቁጥጥር ሥር ዋለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ከመከላከያ ሠራዊት ጥቃት የሸሸ አንድ የጁንታ ሚሊሻ መሪን የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ገልጸዋል።

የሚሊሻ መሪው በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ የመንግሥትን ጦር ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ይፋ አድርጓል።
ለጊዜው ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተረጋግጧል።
የጁንታው አባል በተያዘበት በወቅቱ አምስት ቢሊየን ፓውንድ (ፓውንዱ የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ በይፋ አልተገለጸም)፣ መጠኑ ያልታወቀ ወርቅ፣ የእንጨት ሥራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች አብረውት ተገኝተዋል ተብሏል።

LEAVE A REPLY