የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ኦነግ ሸኔ የሕዝብ ጠላት ነው ሲሉ አወገዙ

የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ኦነግ ሸኔ የሕዝብ ጠላት ነው ሲሉ አወገዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የቦረና አባ ገዳ የሆኑት ኩራ ጃርሶ በምዕራብና በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሽምቅ ጥቃት እየፈጸመ የሚገኘው ኦነግ ሸኔ የሕዝብ ጠላት ነው አሉ።

“እነዚህ ታጣቂዎች የቦረናን ሕዝብ እየገደሉ ነው፤ ለሕዝብ እታገላለሁ የሚል አካል መልሶ ሕዝብን መግደል የለበትም” ያሉት አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ፤  “ኦነግ ሸኔዎች ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ፤ በቦረና ባህል ይህ እጅግ አጸያፊ ነው፣ ባል እያባረሩ ከሚስት ጋር ያድራሉ፣ የጦር መሣሪያ ይነጥቃሉ፣ ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ይገድላሉ፣ ከብት ዘርፈው አርደው ይበላሉ” በማለት ቡድኑ እየደረሰ ነው ያሉትን ድርጊት አውግዘዋል።
ታጣቂ ቡድኑ በተደጋጋሚ በተለያዮ ቦታዎች ሴቶችና ሕጻናትን፣ እንዲሁም አዛውንቶችን መግደሉን ለቢቢሲ የተናገሩት አባ ገዳ ኩራ የሀገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች ታጣቂዎቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ ቢለምኑም ሰሚ እንዳላገኙና አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ከእነርሱ አቅም በላይ እንደሆነ አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY