ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቆጣጠራቸው የትግራይ ክልል ያለምንም እክል እርዳታ እንዲያቀርብ ከስምምነት ላይ መድረሱ ተሰማ።
በተቋሙ ቃሌ አቀባይ ሳቪያኖ አብሬው፤ ስምምነቱ በዚህ ሳምንት ከተፈረመ በኋላ የመጀመሪያው ሥራ የሚሆነው የሚያስፈልጉ የእርዳታ አቅርቦቶችን መገምገም እንደሆነና ይህ ሥራም ረቡዕ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።
ጦርነቱ በተፋፋመበት ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ መንግሥት ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን ለመርዳት የእርዳታ አቅርቦት መስመር እንደሚያመቻችና ከዓለም ዐቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ጋር በጋራ እንደሚሠራ መግለጹ አይዘነጋም።