የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ወደ እስራኤል ተወሰዱ

የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ወደ እስራኤል ተወሰዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አይሁዶች በአውሮፕላን ወደ እስራኤል መጓዛቸውን ቢቢሲ ዘገበ።

እስራኤል ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቤተ እስራኤላውያንን ወደ እየሩሳሌም አመጣለሁ ብላ ቃል ከገባች ሳምንታት በኋላ ይህ እንደሆነ የጠቆመው ዜና፤ ቤተ እስራኤላውያኑ እስራኤል ውስጥ ለዘመናት ከኖሩ አይሁዶች ጋር ዝምድና ያላቸው መሆናቸውን አስረድቷል።
ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል የተከሰተው ጦርነት  ወደ ጎንደር እንዳይዘመትና ቤተ እስራኤላውያን ሰለባ እንዳይሆኑ በመሰጋቱ የእስራኤል መንግሥት ኢትዮጵያዊያን አይሁዶችን ወደ ሀገር ቤት ለማምጣት መወሰኑም ተሰምቷል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ቤኒ ጋንትዝ 316ቱ ቤተ እስራኤላውያን ቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የተቀበሏቸው ሲሆን፤ “ቤተ እስራኤላውያኑን፤ ኢትዮጵያዊያን አይሁድ እህት ወንድሞቻችን ከአውሮፕላን ሲወርዱ በተመለከትን ጊዜ፤ ወርደው የእስራኤልን ምድር ረግጠው ባየን ጊዜ፤ እንባችን መጣ” ሲሉም  ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ተናግረዋል።
ኦፕሬሽን ሮክ ኦፍ እስራኤል የሚል ስያሜ የተሰጠው የቤተ እስራኤላውያኑ ጉዞ ሐሙስ ዕለት የተደረገ ሲሆን ተጨማሪ ቤተ እስራኤላውያን ነገ አርብ ወደ እስራኤል እንደሚወሰዱና በጥር ወር 2021 ደግሞ 1 ሺኅ 700 ትውልደ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች እንደሚጓዙ ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY