የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ አሻሻለ

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ አሻሻለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ ማሻሻሉ ተሰማ።

ዐቃቤ ህግ ቀደም ሲል ያቀረበው ክስ የተጣመረ እና ግልፅ ባለመሆኑ ተሻሽሎ ለዛሬ እንዲቀርብ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት በተሰጠው ቀጠሮ መሠረት ክሱ ተሻሽሎ ቀርቧል።
ቀደም ባለው ጊዜ ዐቃቤ ህግ የወንጀል ህግ 238/1B እና 256ን አጣምሮ አቅርቧል በሚል እንዲያሻሽል መታዘዙን ተከትሎ፤ “አቶ ልደቱ አያሌው በወንጀል ህግ 238 ንዑስ አንቀጽ 1B በመተላለፍ ህገ መንግሥት እና ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሀይል ለመናድ የተለያዩ የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ሰነዶችን አዘጋጅተው እና በፍተሻም ተይዞባቸዋል” በማለት ዐቃቤ ሀግ ክሱን ነጥሎ እና ግልፅ በማድረግ አሻሽሎ ማቅረቡ ታውቋል።
በተሻሻለው ክስ ላይ የአቶ ልደቱ አያሌው ጠበቆች መቃወሚያቸውን በጽሑፍ ለማቅረብ በጠየቁት መሠረት መቃወሚያቸውን ለመመልከት ለታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል።

LEAVE A REPLY