ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ የተካሄደው ጦርነት ማብቃቱንና በአሁን ሰዐት ጥቂት የአሸባሪ ቡድን አባላትን እየተከታተሉ መያዝ ብቻ እንደቀረ አቶ ዛዲግ አብርሃ አረጋገጡ።
“ህወሓት ጦርነት ማድረግ የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና የለውም፣ ወታደር የለውም፣ ትልልቅ መሣሪያዎች የሉትም። የሕዝብ ድጋፍም የለውም” በማለት የተናገሩት የዲሞክራሲ ግንባታ ሚኒስትሩ ዛዲግ አብርሃ፤ አሁን ፌደራል መንግሥቱ አሸባሪዎችን ተከትሎ በመያዝ ሥራ ብቻ እንደተደመጠ አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያንዳንዱን የሚወሰደውን እርምጃ በጥንቃቄ ይከታተሉና መመሪያ ይሰጡ እንደነበር ያስታወቁት አቶ ዛዲግ አብርሃ፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ስትራቴጂ ሲወጣ አንድም ስህተት ላለመሥራት ለይቶ በማጥቃት ወይም በሰርጂካል ኦፕሬሽን ላይ የተመሠረተ በመሆኑ በመንግሥት በኩል የሲቪል ጉዳትን ሙሉ በሙሉ አስወግደናል ሱሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።