ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ተፅዕኖ ፈጣሪዋ ትምኒት ገብሩ ከጉግል ተባረረች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ተፅዕኖ ፈጣሪዋ ትምኒት ገብሩ ከጉግል ተባረረች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተፅእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ባለሙያዎች አንዷ የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ትምኒት ገብሩ ከጉግል ተባርሪያለሁ አለች።

የተቋሙ የሥነ ምግባር ቡድን አጋር መሪ የነበረችው ትምኒት፤ ከጉግል እንደተባረረች ይፋ ባደረገችበት የትዊተር ገጿ፤ በሰው ሠራሽ ልህቀት ዘርፍ ላለው መድልዎ ትኩረት እንዲሰጥና በዘርፉ እምብዛም ውክልና ያላገኙ ሰዎች እንዲቀጠሩ የሚያሳስብ ኢሜል መላኳን ተከትሎ ከሥራ መባረሯ እንደተነገራት አስታውቃለች።
የትምኒትን መባረር በርካታ በሰው ሠራሽ ልህቀትና ተያያዥ የቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚሠሩ እውቅ ባለሙያዎች በትዊተር ላይ ድምጻቸውን እያሰሙም በማስተጋባት ላይ ናቸው።
ጉግል በበኩሉ በሕገ ወጥ መንገድ ሠራተኞች እንዳላባረረ ጠቁሞ፤ ተቋሙ ያወጣው የቅሬታ ደብዳቤ ከዓመት በፊት የተባረሩ አራት ሠራተኞችን የሚመለከት እንደሆነና  ሠራተኞቹ ማኅበር ለማቋቋም የድርጅቱን የስብሰባ አዳራሽ ተጠቅመዋል በማለት ከሥራ እንዳሰናበታቸው አስታውቋል።

LEAVE A REPLY