ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የአትሌቲክስ ዊክሊ መጽሔት ምርጥ ሴት አትሌት ሆና ተመረጠች።
በአትሌቲክስ ላይ የሚዘግበው የእንግሊዙ አትሌቲክስ ዊክሊ መጽሔት፣ ባለፉት 75 ዓመታት ውስጥ ምርጥ አትሌትን እንዲመርጡ ለአንባቢዎቹ ጥሪ ባቀረበው መሠረት፤ ድምጻቸውን ከሰጡ አንባቢዎች መካከል 31.1% የሚሆኑት “የኛ ምርጥ ሴት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ናት” በማለት ድምፅ መስጠታቸው ተገልጿል።
በወንዶች ጃማይካዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ዩሲዬን ቦልት 55.3% በማግኘት የምርጦች ምርጥ አትሌት ተብሎ ሲመረጥ፤ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በ17.1% ድምፅ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል።
ምርጥ አትሌቶቹን ለመምረጥ የተቀመጡ መስፈርቶች አትሌቶቹ ያገኟቸው ሜዳሊያዎች፣ ያስመዘገቡት ክብረ-ወሰን እና የከወኗቸው የማይረሱ አስደናቂ ክስተቶች እንደሆኑ ተገልጿል።