ፓርላማው የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ህግ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያየ

ፓርላማው የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ህግ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያየ

PM Netanyahu addressing the Ethiopian parliament

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በወንጀል ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ህግ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

በ1952 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ ውሎ በ19 96 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣው የወንጀል ት እና የማስረጃ ህግ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ እንዲሆን ያግዛል የተባለው ይህ አዋጅ፣ በቋሚ ኮሚቴው፣ ከህግ ጉዳዮች ጥናት ዳይሬክቶሬት እና ከምክር ቤት የተደረጉ ጥናቶችን ተከትሎ በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህግ ማርቀቅ እና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት አቶ በላይሁን ይርጋ አዲሱ ረቂቅ የህግ ሥነ ሥርዓት ከዚህ ቀደም የነበረውን አሠራር የተፋጠነ እንደሚያደርገው ጠቁመው፤ ይህ ረቂቅ አዋጅ በተለያዩ መድረኮች ውይይት ከተደረገበት በኋላ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ እንደሚፀድቅ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY