ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የብሔራዊ ጀግኖችና የሕጻናት አምባ የበላይ ጠባቂ ሆኑ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የብሔራዊ ጀግኖችና የሕጻናት አምባ የበላይ ጠባቂ ሆኑ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ የብሔራዊ የጀግኖችና የሕጻናት አምባ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ  በብሔራዊ የጀግኖችና የሕጻናት አምባ የቦርድ አባላት  የቀረበላቸውን  ጥያቄ ተቀበሉ።

ፕሬዚዳንቷ የብሔራዊ የጀግኖችና የህጻናት አምባ የቦርድ አባላት ጋር በተወያዮበት ወቅት፤ የቦርዱ አባላት ማኅበሩ የተጎዱ ጀግኖችንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመርዳትና ለመንከባከብ የተቋቋመ  መሆኑን በማስረዳት ነበር ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ የማህበሩ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ ጥያቄ ያቀረቡት።
ጀግኖችን መንከባከብ የማህበረሰብ ግዴታ መሆኑን ያስረዱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የበላይ ጠባቂነት ጥያቄዉን  መቀባላቸውን በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ትስስር  ገጽ ካሰራጩት መረጃ መገንዘብ ተችሏል።

LEAVE A REPLY