ቆላ ተምቤን የመሸጉት እነደብረፂዮን ላይ 31ኛው ክፍለ ጦር ምሽግ የማስለቀቅ እርምጃ እየወሰደ...

ቆላ ተምቤን የመሸጉት እነደብረፂዮን ላይ 31ኛው ክፍለ ጦር ምሽግ የማስለቀቅ እርምጃ እየወሰደ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ከተለያዮ አካባቢዎች ሸሽቶ ቆላ ተምቤን ሀገረ ሰላም የመሸገው የጁንታው ቡድን አመራሮች ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት 31ኛው ክፍለ ጦር ምሽግ የማስለቀቅ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ይፋ አደረገ።
በ31ኛ ክፍለጦር ምክትል አዛዥና ወጊያውን የሚመሩት ኮሌኔል ሻምበል በየነ፤ የመሸጉት የህወሓት ጁንታ አመራሮችና አባላት ምንም የማምለጫ ቦታ እንደሌላቸውም ገልጸዋል።
ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች የትህነግ ቡድን አመራሮች፣ የቀድሞው የ31ኛው ክፍለ ጦርን ይመራ የነበረው ጄነራል ከበደ በመሸጉበት ስፍራ ተከበው እንደሚገኙም ተነግሯል።
የህግ ማስከበር ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን እና የአካባቢው ነዋሪዎችም በዚሁ ሥራ ላይ ተሳታፊ መሆኑን የጠቆሙት አዛዡ፤ አሁን ላይ ቀሪ የሚባሉት የዚህ ድርጊት ተሳታፊ ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ ሥራ በትክክለኛው መንገድ እየተፈጸመ ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY