ሄሎ ታክሲ በትግራይ ክልል ባለው ችግር ምክንያት የ3ኛ ዙር ተሽከርካሪዎችን ማስረከብ አልቻልኩም...

ሄሎ ታክሲ በትግራይ ክልል ባለው ችግር ምክንያት የ3ኛ ዙር ተሽከርካሪዎችን ማስረከብ አልቻልኩም አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ችግር ምክንያት ሄሎ ታክሲ ለሦስተኛ ዙር የሚያስረክባቸውን ተሽከርካሪዎች  ማስረከብ አለመቻሉን አስታወቀ።

ክላውድ ወርልድ ዋይድ ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ሄሎ) ታክሲ እንደገለጸው ከሆነ መኪናዎቹን የሚገጣጥመው ኦክሎክ ጀነራል ሞተርስ አንደኛው መገጣጠሚያ ፋብሪካ  በትግራይ ክልል የሚገኝ በመሆኑ፤ አሁን በክልሉ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ መስተጓጎል መፍጠሩን እና ለማስረከብ መቸገሩን ገልጿል።
ይህን ተከትሎም የሄሎ ታክሲ ባለቤት እና ሥራ አስፈፃሚ ከሀገር ጠፍተዋል በሚል ወሬ እንዲነዛ እና ሆነ ተብሎ ስም የማጥፋት ሥራም እየተሠራ እንደሚገኝ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ዳንኤል ዮሐንስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY