መንጋና ጽንፈኞች ባወደሟት ሻሸመኔ ከተማ የእርቅ ጉባኤ መካሄድ ተጀመረ

መንጋና ጽንፈኞች ባወደሟት ሻሸመኔ ከተማ የእርቅ ጉባኤ መካሄድ ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በተለያዮ ጊዜያት በመንጋ እና ጽንፈኛ ብሔርተኞች ጥቃት ከፍተኛ ውድመት በደረሰባት የኦሮሚያ ክልሏ ሻሸመኔ ከተማ የእርቅ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

የእርቅ ጉባኤ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ከከተማዋ አስተዳደር እና ከኖርዌይ ቤተክርስትያን የእርዳታ ድርጅት ጋር በመተባር ያዘጋጁት ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ የሃይማኖት መሪዎች፣ አባ ገዳዎች እና አደ ሲንቄዎች ተሳትፈዋል።
ከወራት በፊት በኦሮሚያ ክልል በተፈጠሩ ሁከት የተጎዱ መኖሪያ ቤቶች በነዋሪው ትብብር መልሰው መገንባታቸው በውይይቱ ላይ ተገልጿል። ሻሸመኔ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ሙሉሙሉ የተመለሰች ሲሆን፤ በከተማዋ ተፈጥሮ በነበረው ሁከት ላይ እጃቸው አለበት የተባሉ 600 ሰዎች ጉዳያቸው በህግ እየታየ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY