በአዲስ አበባ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከ2 ሺኅ 300 በላይ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች...

በአዲስ አበባ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከ2 ሺኅ 300 በላይ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ተገነቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ከተማ የ2013 የትምህርት ዘመን ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የገጽ ለገጽ ትምህምርት ዛሬ ኅዳር 28/2013 ም/ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መካኒሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት በይፋ አስጀምረውታል።

ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ልዩ ጥንቃቄ ለማድረግ ከ2ሺህ 300 በላይ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እና 118 የመመገቢያ አዳራሾች በከተማዋ ትምህርት ቤቶች መገንባቱ ተነግሯል።
 በትምህርት ማስጀመር መርሐ ግብር ላይ የተገኙት አዳነች አቤቤ ለተማሪዎች የተዘጋጀ ዩኒፎርም ፣የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና የተለያዩ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ፤ለመምህራን ደግሞ የጋውን ስጦታ አበርክተዋል።

LEAVE A REPLY